የምናቀርባቸው አገልግሎቶች

Agricultural Products

የግብርና ምርቶች

ዘላቂ የግብርና አሰራሮችን ለመደገፍ እና የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የግብርና ምርቶችን እናቀርባለን። የእኛ አቅርቦቶች የገበሬዎችን እና የግብርና ንግዶችን ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጁ ዘሮችን፣ ማዳበሪያዎችን እና የተለያዩ የሰብል ጥበቃ መፍትሄዎችን ያካትታሉ።

በተጨማሪም፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ጤናን እና የተመጣጠነ ምግብን በማስተዋወቅ የተለያዩ ፍረሽ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን እናቀርባለን። ትኩረታችን ለንግድ ግብይት የሀገር ውስጥ አርሶ አደሮች እና አምራቾች ሰፊ ገበያ እንዲያገኙ በማድረግ ኑሯቸውን ማሳደግ ነው።

Detergents & Soaps

ዲተርጀንትና ሳሙናዎች

ጤናማ የሆኑ ፣ ውጤታማ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የጽዳት ምርቶች ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ናቸው። የኢንዱስትሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሳሙናዎችንና ዲተርጀንቶችን እናቀርባለን።

Commission Agency Services

የኮሚሽን ኤጀንት አገልግሎቶች

የኛ የኮሚሽን ኤጀንሲ አገልግሎቶች አምራቾች እና አቅራቢዎች የታለመላቸው ገበያ ላይ እንዲደርሱ በማድረግ ጥራት ያላቸውን ምርቶች የገበያ ተደራሽነት ያመቻቻል።

ቁልፍ ባሃሪያቶች:

  • አስተማማኝ የአቅርቦት ሰንሰለት: ወቅታዊ አቅርቦትን እና የምርት አቅርቦትን የሚያረጋግጡ ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እና የማከፋፈያ መረቦችን እናቀርባለን።
  • የምርት ጥራት ማረጋገጫ: ደንበኞቻችን ለሚፈጽሙት ግዢ ጥራት ሳይጨነቁ የአእምሮ ሰላም እንዲያገኙ የጥራት ማረጋገጥ አገልግሎት እንሰጣለን።
  • ቀጣይነት ያለው የንግድ ስርአት: በስራዎቻችን እና በአጋሮቻችን መካከል ዘላቂነት ያለው አሰራርን እናበረታታለን እንዲሁም እናስተዋውቃለን።
  • የረጅም ጊዜ ሽርክናዎችን መገንባት:የጋራ ጥቅሞችን ለመፍጠር እና ስኬትን ለማምጣት ከደንበኞቻችን፣ ባለድርሻ አካላት እና አቅራቢዎች ጋር ጠንካራ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ግንኙነቶችን በማፍራት እናምናለን።
Asset Security

የንብረት ደህንነት

የእኛ የንብረት ደህንነት አገልግሎቶች የእርስዎን ጠቃሚ ሀብቶች ለመጠበቅ የተዘጋጁ ናቸው። የአደጋ ምዘናዎችን፣ የደህንነት እቅድ ማውጣትን እና ለእርስዎ ልዩ ፍላጎቶች የተዘጋጁ የደህንነት እርምጃዎችን መተግበርን ያካተቱ አጠቃላይ መፍትሄዎችን እናቀርባለን።

ቁልፍ ባህሪያት:

  • የአደጋ ግምገማ: በንብረቶችዎ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋና እና ስጋቶችን ለመለየት ጥልቅ ግምገማዎችን እናደርጋለን።
  • ምቹ የደህንነት መፍትሄዎች: ቡድናችን አካላዊም ሆነ ዲጂታል ንብረቶችን ለመጠበቅ ምቹ የደህንነት ስልቶችን ያዘጋጃል።
  • ክትትል እና ድጋፍ:ማንኛውንም የደህንነት ስጋቶች በፍጥነት እና በብቃት ለመፍታት የማያቋርጥ ክትትል እና ድጋፍ እንሰጣለን።
  • ስልጠና እና ግንዛቤ: ሰራተኞቻችሁ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር አስፈላጊ የሆኑትን እውቀት እና ክህሎቶች ለማስታጠቅ የስልጠና ፕሮግራሞችን እንሰጣለን።

Scroll to top